top of page

በማንነታቸው ከአጣየ  ከመተከል  ከጉራፈረዳ እና ሌሎች ቦታዎች ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ለወደቁ ወገኖች እንዲሁም የህወሐትን ቡድን ለህግ ለማቅረብ በተደረገው ህዝባዊ እና መንግስታዊ ዘመቻ ተሳትፈው አካላቸው ለጎደለ ፣ የህይወት መስዋትነት ለከፈሉ ጀግኖች፣ እና  ቤተሰቦች እንድረስ ከጎናቸውም እንቁም ስንል ውድ ህይወቱን ለመስጠት በማይሳሳው የዐማራ ህዝብ ሰም እንለምናለን።

የዚህ የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ምክንያት በወሎና በሸዋ ለተፈናቀሉ አማራ አርሶ አደሮች ለምግብ፣ለልብስ፣ለመጠለያና ለመልሶ ማቋቋም ስራዎች ይውላል። እርስዎም የአቅምዎን ለወገንዎ በመለገስ ድጋፍዎትን ይግለጹ።

የአማራው ሐዘን የኔም ሐዘን ነው በማለት ከአማራ ህዝብ ጎን ስለቆሙ ከልብ እናመሰግናለን።

በኦሮሚያ ክልል (ከወለጋ) ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ይለግሱ

ይህ ገንዘብ የማሰባሰብ ህብረት የተቋቋመው ከኦሮሚያ ክልል (ወለጋ) በሚደርስባቸው ግድያ እና ስቃይ በመሸሽ በድንገት ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ወሎ በተለይም ሃይቅ እና ጃሪ ለተጠለሉ ንጹሃን ወገኖቻችን የመልሶ ማቋቋም ስራ ታስቦ ሲሆን በአሁኑ ሰአት የችግሩ ሰለባዎች በቂ የሆነ የምግብ፡ አልባሳትና መጠለያ አቅርቦት የላቸውም፡፡ በርካታ ተፈናቃዮች ለህይወታቸው በመስጋትና መጠለያ ለማግኘት ሲሉ ወደ ደቡብ ወሎ በመምጣት ላይ ስለሚገኙ የሰብአዊ ቀውሱ ሊባባስ ከመቻሉም ባሻገር አሁን ባለው ሁኔታ ከቀጠለ ወገኖቻችን ለተጨማሪ የኮሮና ወረርሽኝ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ 

የአማራ ማኅበር በአሜሪካ የተመሰረተው ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊ የሲቪክ ድርጅት ሲሆን ተልዕኮው በአሜሪካ ውስጥ የሚገኙ አማራዎችን ማሳወቅ ፣ ማደራጀትና ማጎልበት በመሆኑ በሀገራችንም ውስጥ ለታሪካዊው የአማራ ንቅናቄ አስተዋፅዖ እያበረከት ይገኛል ፡፡

bottom of page